የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ እና 5ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ
የአዲስ-አፍሪካ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል አ.ማ የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ እና 5ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔዎች ቅዳሜ ሕዳር 24 ቀን 2009 ዓ.ም ካዛንቺስ በሚገኘው ኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የመታወቂያ ወረቀት በመያዝ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ የስብሰባዎቹ አጀንዳዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1. ድምጽ ቆጣሪዎችንና የጉባዔውን ጽ/ቤት መሰየም
2. የጉባዔውን ረቂቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ማጽደቅ
3. የዲሬክተሮች ቦርድን የ2008 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ማድመጥ
4. የውጪ ኦዲተሮችን የ2008 በጀት ዓመት የሂሳብ ሪፖርት ማድመጥ
5. በዲሬክተሮች ቦርድ እና በውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ
6. በኩባንያው የተፈረመ ካፒታል አሰባሰብ ላይ ተወያይቶ መወሰን
7. በጎደሉ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምትክ አዲስ የዲሬክተሮች ቦርድ አበላትን መሰየም
8. የኩባንያውን የውጪ ኦዲተሮች ቅጥር ተመልክቶ ማጽደቅ
9. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ
የድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1. ድምጽ ቆጣሪዎችንና የጉባዔውን ጽ/ቤት መሰየም
2. የጉባዔውን ረቂቅ መነጋገሪያ አጀንዳ ማጽደቅ
3. የኩባንያውን መመሥረቻ ጽሑፍና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል
4. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ
ማሳሰቢያ፦
በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከሚካሄድበት ዕለት ሦስት የሥራ ቀናት በፊት ቦሌ መድሃኒዓለም፣ መድሃኒዓለም ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመፈረም ወይም በሌላ ሕጋዊ መንገድ ውክልና በተሰጠው ግለሰብ አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
የአዲስ-አፍሪካ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል አ.ማ የዲሬክተሮች ቦርድ